about us
about us
ስለ እኛ
እኛ ማን ነን
አፍሪካ አካዳሚ ኢስላማዊ ትምህርትን በአማርኛ ቋንቋ፣ ሙሉ በሙሉ በነፃ እና በርቀት (Online) የሚሰጥ ተቋም ነው። ዋና ዓላማውም አማርኛ ተናጋሪ ሙስሊም ማህበረሰብን የእስልምናን ትክክለኛ ግንዛቤ ከቁርኣን እና ከሱና ማግኘት እንዲችሉ ማስቻል ነው።
አካዳሚው 100% በኢንተርኔት (Online) ላይ የተመሰረተ ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፥ ዕውቀትን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ለማቅረብ ማህበራዊ ሚዲያዎችን፣ የኢንተርኔት አማራጮችን እና የአፍሪካ ቲቪ (Africa TV) ሳተላይት ቻናልን በስፋት ይጠቀማል። ይህንን ተደራሽነት እውን ለማድረግም ዘመናዊ የኦንላይን ማስተማሪያ ስልቶችን (MOOCs)፣ የኤሌክትሮኒክስ መማሪያ ቁሳቁሶችን እና በአማርኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ ታዋቂና እውቅ የኡለማኦችን እንዲሁም የአካዳሚክ ባለሙያዎችን ስብስብ አዋቅሮ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ተልዕኳችንና ራእያችን
ተልዕኮ
አዳዲስ የቴክኖሎጂ ስልቶችን፣ የሳተላይት ስርጭቶችን እና የተለያዩ የኦንላይን ዌብሳይቶችን በቅንጅት በመጠቀም፤ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚሰጡ የዲጂታል (ኢ-ለርኒንግ) ትምህርቶች ግንባር ቀደም እንዲሁም የላቀ እና መሪ አካዳሚ መሆን
ራእይ
በመጀመሪያዎቹ ሦስት ዙሮች ውስጥ በክፍት የትምህርት ሥርዓታችን አማካኝነት 70,000 ተጠቃሚዎችን ለመድረስ እንመኛለን።
ዓላማዎቻችን
ማንኛውም ሙስሊም የግድ ሊያውቃቸው የሚገቡትን እና የእስልምና እውቀት ፈላጊዎች ሁሉ ሊገነዘቧቸው የሚገቡ መሰረታዊ የዲን እውቀቶችን በአፍሪካ ቋንቋዎች ተደራሽ በማድረግ የማህበረሰቡን የእውቀት ጥማት ማርካት
የአህለ ሱና ወልጀማዓ ዓቂዳንና ትክክለኛውን ፍቅህ ከቁርኣንና ከሱና ማስረጃዎቹ ጋር ማስፋፋት።
ሙስሊም ሴቶችን ሃይማኖታቸውን ማስተማር፣ ግንዛቤያቸውን ማሳደግና የሴት የእስልምና ዕውቀት ተማሪዎችን ለማዘጋጀት መርዳት።
አቀራረቡ ሙያዊ ብቃትን እና ፈጠራን ያማከለ የትምህርት ሥርዓት በማቅረብ፤ በአፍሪካ ውስጥ በኢስላማዊ ትምህርቶች የኢ-ለርኒንግ (የኦንላይን) ትምህርት ባህልን ማስፋፋት

