Last modified: Monday, 16 November 2026, 5:25 PM
ይህ ገጽ የአፍሪካ አካዳሚ መተግበሪያን እና ድረ-ገጹን am.africaacademy.com ይመለከታል። በማንኛውም ጊዜ መለያዎ እና ሁሉም የግል መረጃዎ እንዲሰረዝ መጠየቅ ይችላሉ።
ጥያቄው ነፃ ነው፤ ምክንያት መግለጽም አያስፈልግም።
1. በድረ-ገጹ በኩል የሚጠየቅበት መንገድ
- መለያዎን በፈጠሩበት መንገድ (በጉግል ወይም በቴሌግራም) ከመግቢያ ገጹ ይግቡ።
- ከገቡ በኋላ የመረጃ መሰረዣ ጥያቄ ገጹን ይክፈቱ።
- «ሁሉንም የግል መረጃዬን ሰርዝ» የሚለውን ይምረጡ፣ ከዚያ «ለውጦችን አስቀምጥ» የሚለውን ይጫኑ።
2. በመተግበሪያው በኩል የሚጠየቅበት መንገድ
- «የተጠቃሚ መለያ» የሚለውን ለመክፈት በማያ ገጹ አናት ላይ ያለውን ፎቶዎን ይጫኑ።
- «የመረጃ ግላዊነት» የሚለውን ይምረጡ፣ ከዚያ «ሁሉንም የግል መረጃዬን ሰርዝ» የሚል አዲስ ጥያቄ ይፍጠሩ።
3. የሚሰረዘው ምንድን ነው
- መለያዎ እና የመገለጫ መረጃዎ፤ ለምሳሌ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር እና ፎቶ።
- ጥያቄው ከተፈጸመ በኋላ በዚህ መለያ መግባት አይችሉም፤ መለያውንም መመለስ አይቻልም።
4. ሊቀር የሚችለው ምንድን ነው
- በመወያያ መድረኮች ላይ የጻፏቸው መልዕክቶች ይዘታቸው ይሰረዛል፤ በስምዎ ቦታም «የተሰረዘ ተጠቃሚ» ይታያል።
- በትምህርት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያከሏቸው አንዳንድ ይዘቶች ከስምዎ ጋር ሳይያያዙ ሊቀሩ ይችላሉ።
5. ያግኙን
ወደ መለያዎ መግባት ካልቻሉ ወይም እገዛ ከፈለጉ ያግኙን፦
የግላዊነት ፖሊሲ
Last modified: Monday, 16 November 2026, 5:32 PM