“የ አፍሪካ አካዳሚ ትክክለኛውን እስላማዊ ግንዛቤ ቁርአን እና ሃዲስን በምንጭነት በመጠቀም ለ አፍሪካ ማህበረሰብ የሚያቀርብ የርቀት ትምህርት ነው ፡፡የ ትምህርት ፕሮግራም ቀርጾ ለ እውቀት ፈላጊዎች በ ኢንተርኔት በ ማህበራዊ ድህረ ገጾች እና በ አፍሪካ ቲቪ ማቅረብን አላማ ያደረገ ነው፡፡የ ርቀት ትምህርቱንም አካዳሚያችን የ ሚጠቀመው ኮርሶቹን በ ቀላሉ እና በ ኦንላይን ማድረስ በአጭሩ (Massive Open Online Course)አካዳሚያችን 100% ኤሌክትሮኒክስ ሲሆን በማን ኛውም ወቅት ተማሪው በ ኮምፑዩተር ወይም በ ስማርት ስልክ ገብቶ መከታተል ይችላል ፡፡ ትምህርቶቹን እንዲሁም መልመጃዎችን በቀላሉ ሊገለልገሉ ይችላሉበ አፍሪካ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ አህለሱና ወልጀመአ መምህራኖችን አካዳሚያችን አካቷል፡፡”
በመጀመሪያዎቹ ሦስት ክፍሎች 30 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በርቀት የትምህርት ሥርዓቱ ይሳተፋሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
አካዳሚያችን በ ቲቪ እና በ ማህበራዊ ድህረ ገጽ በዘመናዊ እና ጊዜውን ባማከለ መልኩ በተለያዩ የ አፍሪካ ቋንቋዎች ትምህርትን የሚያቀርብ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ የሚገኝ መሪ አካዳሚ መሆን፡፡
1- የሙስሊሞችን መሰረታዊ የሸሪአ ትምህርት ክፍተትን በመሙላት ማንኛውም ሙስሊም ተማሪ ሊያውቀው የሚገባ እውቀትን በአፍሪካ ቋንቋዎች ማቅረብ ነው ፡፡2- የ አህለሱና ወልጀመዓ አስተሳሰብን ትክክለኛውን የፊቂህ ግንዛቤ ከቁርአንና ከሃዲስ ማስረጃዎች በማጠናቀር3- ሙስሊም ሴቶችን ስለ ዲን ማስተማር ፣ ግንዛቤን ማሳደግ እና ማስተማር እንዲሁም ተማሪዎችን ለሸሪአ ትምህርት በማዘጋጀት አስተዋፅኦ ማድረግ።4- በአቀራረብ ዘዴዎች ውስጥ ሙያዊነትን እና ፈጠራን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሳይንሳዊ ሥርዓተ-ትምህርት በማቅረብ በአፍሪካ ውስጥ በኤሌክትሮኒክስ የ ሸሪአ ትምህርትን ባህል ማሰራጨት።