ከእኛ ጋር ይተዋወቁ

“የ አፍሪካ አካዳሚ ትክክለኛውን እስላማዊ ግንዛቤ ቁርአን እና ሃዲስን በምንጭነት በመጠቀም ለ አፍሪካ ማህበረሰብ የሚያቀርብ የርቀት ትምህርት ነው ፡፡
የ ትምህርት ፕሮግራም ቀርጾ ለ እውቀት ፈላጊዎች በ ኢንተርኔት በ ማህበራዊ ድህረ ገጾች እና በ አፍሪካ ቲቪ ማቅረብን አላማ ያደረገ ነው፡፡
የ ርቀት ትምህርቱንም አካዳሚያችን የ ሚጠቀመው ኮርሶቹን በ ቀላሉ እና በ ኦንላይን ማድረስ በአጭሩ (Massive Open Online Course)
አካዳሚያችን 100% ኤሌክትሮኒክስ ሲሆን በማን ኛውም ወቅት ተማሪው በ ኮምፑዩተር ወይም በ ስማርት ስልክ ገብቶ መከታተል ይችላል ፡፡ ትምህርቶቹን እንዲሁም መልመጃዎችን በቀላሉ ሊገለልገሉ ይችላሉ
በ አፍሪካ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ አህለሱና ወልጀመአ መምህራኖችን አካዳሚያችን አካቷል፡፡”

ራዕይ(ህልማችን)

በመጀመሪያዎቹ ሦስት ክፍሎች 30 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በርቀት የትምህርት ሥርዓቱ ይሳተፋሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

መልዕክት

አካዳሚያችን በ ቲቪ እና በ ማህበራዊ ድህረ ገጽ በዘመናዊ እና ጊዜውን ባማከለ መልኩ በተለያዩ የ አፍሪካ ቋንቋዎች ትምህርትን የሚያቀርብ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ የሚገኝ መሪ አካዳሚ መሆን፡፡

ዓላማዎች(ግቡ)

1- የሙስሊሞችን መሰረታዊ የሸሪአ ትምህርት ክፍተትን በመሙላት ማንኛውም ሙስሊም ተማሪ ሊያውቀው የሚገባ እውቀትን በአፍሪካ ቋንቋዎች ማቅረብ ነው ፡፡
2- የ አህለሱና ወልጀመዓ አስተሳሰብን ትክክለኛውን የፊቂህ ግንዛቤ ከቁርአንና ከሃዲስ ማስረጃዎች በማጠናቀር
3- ሙስሊም ሴቶችን ስለ ዲን ማስተማር ፣ ግንዛቤን ማሳደግ እና ማስተማር እንዲሁም ተማሪዎችን ለሸሪአ ትምህርት በማዘጋጀት አስተዋፅኦ ማድረግ።
4- በአቀራረብ ዘዴዎች ውስጥ ሙያዊነትን እና ፈጠራን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሳይንሳዊ ሥርዓተ-ትምህርት በማቅረብ በአፍሪካ ውስጥ በኤሌክትሮኒክስ የ ሸሪአ ትምህርትን ባህል ማሰራጨት።